Monday, July 22, 2013

Muhamad’s Ill-treatment towards His Wives


Written by emnet123
Edited by MercifulGod
 
የዚህ ጽሁፍ ይዞታ መሐመድ በሚስቶቹ ይ ያደርግ የነበረው ግፍ ያሳየናል።

የመጀመርያ ሚስቱ ከዲጃ ከሞተች በኃላ መሐመድ አራት ሴት ልጆቹን ለብቻው ማሳደግ ስለከበደው፥ ይህም በጊዜው ለወንድ ልጅ በጣም ከባድ ፈተና ስለነበር፥ ችግሩን የተመለከተ ጓደኛው ሳውዳ ቢንት ዛማ የተባለችን ሴት እንዲያገባ ይመክረዋል። ሳውዳ ባልዋ የሞተባት፣ ከመሐመድ በእድመ እኩያ የነበርች፣ ምንም ደጋፊ ያልነበራትና በአባትዋ ስር ትኖር የነበረች ሴት ነበረች። መሐመድ በጓደኛው ምክር በህጉ መሰረት አባትዋን ጠይቆ ህጋዊ ጋብቻ አድርጎ እቤቱ ገብታ ትዳር ተጀመረ።  ለአራት ሴት ልጆቹ እንደ እናት ሆና በማሳደግ በመካ ከተማ አብረው ይኖሩ ነበር።  ከመካ ወደ መዲና ከተሰደደ በኃላ የመሐመድ ህይወት ተቀየር። ዝናንና ሃይልን እየጨመረ በመምጣቱ ብዙ ወጣትና ውብ ሴቶችን ማግባትና የራሱ ማድረግ ጀመረ። በዚህ ምክንያት ሳውዳ ቢንት ዛማን ጣል ጣል በማድረጉና ሊፈታት እንደሆነ የተረዳችው ሳውዳ ለመሐመድ እንዳይፈታት ይልቁንም ከእርስዋ ጋር የሚያሳልፍበትን ለሊት ማለት ተራዋን በወጣትነቱዋና በቁንጅናዋ በጣም ለሚወዳት ለሚስቱ ለአይሻ እንደምትሰጥ ሃሳብ አቀረበች። መሐመድ ከሁሉም ሚስቶቹ በላይ በጣም አብልጦ ከሚወዳት አይሻ ጋር የሚያሳልፈውን ጊዜ ስላስረዘመለት በዚህ ሃሳብ ተስማምቶ በእድሜ ጠና ያለችውን ሚስቱን ሳይፈታ ከእርስዋ ጋር ያለውን ስጋዊ ግንኙነት አቋርጦ የእስዋን ተራ በእይሻ ቤት ያሳልፍ ነበር። አይዞሽ ሳውዳ ስቸገር አብረሽ ተቸግረሽ አሁን ዝናንና ክብርን ሳገኝ እኔን ስለማትመጥኝኝ አንችን ልፈታ አይገባኝም ከማለት ይልቅ ለሳውዳ ያሳየውን ይህን ቀዝቃዛ ስሜት መሐመድ አምላኩ አላህ እንዳጸደቀለትና ቃል እንዳወረደለት ለተከታዮቹ አስተምሮዋል። እስኪ ይህንን ጉዳይ ከቁራንና ከሃዲስ ማስረጃዎችን እንመልከት።

ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 4128 “ሴትም ከባልዋ ጥላቻን፣ ወይም ፊቱን ማዞርን ብታውቅ፣ በመካከላቸው መስማማትን ቢስማሙ፣ በሁለቱ ላይ ኀጢአት የለም። መታረቅም መልካም ነው። ነፍሶችም ንፍገት ተጣለባቸው። መልካምም ብትሰሩ፣ ብትጠነቀቁም፣ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው።”  መሐመድ ይህ የቁርአን ክፍል 4128 ከአላህ ወረደልኝ ያለው ሳውዳ ቢንት ዛማ ፍችን ፈርታ ከመሐመድ ጋር ስምምነትን ባደረገችበት ጊዜ ነበር። ሱራ 4128 አስመልክቶ የሙስሊም ሙህራኖች እንደሚከተለው ይገልጻሉ።

ከ ታፍሲር ኢብን ካቲር የተወሰደAbu Dawud At-Tayalisi recorded that Ibn `Abbas said, "Sawdah feared that the Messenger of Allah might divorce her and she said, `O Messenger of Allah! Do not divorce me; give my day to `A'ishah.' And he did, and later on Allah sent down, (And if a woman fears cruelty or desertion on her husband's part, there is no sin on them both)... At-Tirmidhi recorded it and said, “Hasan Gharib. In the Two Sahihs, it is recorded that `A'ishah said that when Sawdah bint Zam`ah became old, she forfeited her day to `A'ishah, and the Prophet used to spend Sawdah's night with `A'ishah. There is a similar narration also collected by Al-Bukhari. http://www.qtafsir.com/index.php?option=com_content&task=view&id=599&Itemid=59

ኢብን አባስ የተናገረውን አቡ ዳውድ አት ታያሊሲ እንደዘገበው፦ “የአላህ መልክተኛ ይፈታኛል ብላ ሳውዳ በመፍራትዋ እንዲህ አለችው፥ ‘ኦ የአላህም መልእክተኛ! እባክህን አትፍታኝ፣ ከእኔ ጋር የምታሳልፈውን ቀኔን ለአይሻ ስጣት። እሱም አደረገው፥ በኋላም አላህ ቃሉን ላከ፥ (ሚስት ከባልዋ ጭካኔንና መገፋትን ብትፈራ፥ በሁለቱም ሃጥያት የለባቸውም) ,,, አል ትርሚዲ እንደዘገበው፥ “ሃሰን ጋሪብ በሁለቱ ሳሂህ እንደምናገኘው አይሻ ስትናገር የሳውዳ ቢንት ዛማህ እድሜ በገፋ ጊዜ ቀኑዋን ለአይሻ አሳልፋ በመስጠትዋ ነብዩ የሳውዳን ምሽት ከአይሻጋር ያሳልፍ ነበር።” በአል-ቡኋሪ የተሰበሰበ ሌላም ተመሳሳይ ሃዲስ ይገኛለ።

ብዙ ተጨማሪ ሃዲ(የመሃመድ ድርጊቶችና ንግግሮች ስብስብ) እንደማረጃነማቅረብ ይቻላል ለምሳሌ የሚከተለውን ሃዲስ እንመልከት።

Narrated Aisha: … Sauda bint Zam’a gave up her (turn) day and night to ‘Aisha, the wife of the Prophet in order to seek the pleasure of Allah's Apostle (by that action). (Sahih Al-Bukhari, Volume 3, Book 47, Number 766) (Also, see Sahih Muslim, Book 008, Number 3451)

አይ እንደተረከችው፦ ,,, ህን መልእክተኛ ለማስደሰት ስትል ሳውዳ  ቢንት ዛማ መልእክተኛው የሚጎበኛትን ቀን ተራዋን ለአይሻ አሳልፋ ሰጠች። (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 3 መጽሃፍ 47 ቁጥር 766) (ሂህ ሙስሊም መጽሃፍ 008 ቁጥር 3451)

ለሌሎ ታላቅ ምሳሌ ለመሆን ተጠርቻለሁ ያለው መሐመድ ችግሩ ጊዜ ያገለገለችውን ሚስቱን እንደ አሮጌ እቃ መቁጠሩና  ይህንንም ድርጊቱን አላህ አጽድቆልኛል በማለት ይህን ግፍ ተከታዮቹም በሚስቶቻቸው ላይ እንዲፈጽሙ መፍቀዱ በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው። የተጨነቀችና የፈራች ሚስቱን ምንም ብታረጅና ውበትዋ ቢቀንስም አይዞሽ አልፈታሽም ከአንችም ጋር የማሳልፈውን ቀን ለማንም አልሰጥም ብሎ ሊያጽናናት አይገባምን? በችግሩ ጊዜ አብራ የተቸገረችውን ዝናንና ስልጣንን እንዲሁም ወጣትና ቆነጃጅት ሚስቶችን ባገኘ ጊዜ እንዳረጀች እቃ መቁጠር ይህ ምን አይነት ስነምግባር ነው?

No comments:

Post a Comment