Sunday, April 15, 2012

Testing a Prophet - ነብይን መፈተን :- ነብይ ነኝ ብሎ የተነሳን ሰው ሁሉ ያለጥርጣሬ ይቀበሉታልን?


ብይ ነኝ ብሎ የተነሳን ሰው ሁሉ ያለጥርጣሬ ይቀበሉታልን?
መግቢያ

እስልምና ነቢይ ነኝ ብሎ በ7ኛው ክፍለ ዘመን የተነሳውን መሐመድን በመደገፍ ክርስትናንና መጽሐፍ ቅዱስን ማጥቃት ከጀመረ ጊዜያት አልፈዋል። የእምነቱ ተከታዮች በክርስትና ላይ ያላቸውን የተሳሳተ ግንዛቤ እንዲያስተውሉ ለመርዳት ያህልና ስለእስልምና ያለንን አቋም ለሁሉ ግልጽ ለማድረግ የእስልምና ምንጭ የሆነውን የመሐመድን ማንነት ለማጥናት ወስነናል። መሐመድ የእስልምና እምነት መስራች ሲሆን ተከታዮቹም እንደነብይ ይቆጥሩታል። በዚህ ጽሁፍ መሐመድ ነብይ ነው የሚለውን ትምህርት እንገመግማለን።

እግዚአብሄር መንፈስንና ነብያትን ከእርሱ የተላኩ ለመሆናቸው የህይወት ዘይቤአቸውን፣ ፍሬአቸውንና ባጠቃላይ ሊመዘን የሚገባውን ማንኛውንም ነገር እንድንፈትን አዞናል (ማቴዎስ ወንጌል 7፡15-16 ና 24:24-25፣ 1ኛ ተሰሎንቄ 5፡19-22፣ 1ኛ ዮሐንስ 4፡1፣ 2ኛ ቆሮንጦስ 11፡14)።

ክርስትያኖች እግዚአብሄር ነብያቶችን እንደሚልክ ስለሚያምኑ መሐመድ የእግዝአብሄር ነብይ ሊሆን አይችልም ባንልም፤ ይህ ማለት ግን ማንም ሰው በጭፍን የመሐመድን ነብይነት ይቀበላል ማለት አይደለም። እንዲህ ቢሆን ግን ሞኝነትና አለመታዘዝ ነው። ይልቁንም ነብያት ከእግዝአብሄር መሆናቸውንና አለመሆናቸውን እንድንፈትን ታዘናል።  ስለዚህ መሐመድ እውነተኛ ወይም ሀሰተኛ ነብይ መሆኑን ልንመረምር ይገባል። በዚህ ጽሁፍ የመሐመድን ትምህርቶች፣ የፈጸማቸውን ድርጊቶች፣ እንዲሁም የተናገረውን ትንቢቶች በቁርአን፣ በሃዲት (መሐመድ ያደረጋቸውና የተናገራቸው ነገሮች ተሰብስበው የተጻፉበት መጽሃፍ) እና የመሐመድ የሕይወት ታሪክ መጻህፍቶችን ከመጽሃፍ ቅዱስ ጋር በማስተያየት የመሐመድን እውነተኛ ነብይነት እንገመግማለን።

መሐመድ እውነተኛ የእግዚአብሄር ነብይ ነውን?

1)    የመሐመድ አስተምህሮና ስነምግባር

ቁርአን የአይሁድንና የክርስቲያኖችን መጽሀፍት የሚያረጋግጥ እንደሆነ ሲያውጅ መሐመድም የነብያትን ፈለግ እንደተከተለ ይናገራል። ለመሆኑ ቁርአን መጽሃፍ ቅዱስን ያረጋግጣልን? መሐመድስ የቀደሙ ነብያትን ፈለግ ተከትሎአልን?
ቁርአን /ምእራፍ 4፡47 ,,, በፊት ከእናንተ ጋር ያለውን የሚያረጋግጥ ኾኖ ባወረድነው (ቁርአን) እመኑ ,,,
ቁርአን /ምእራፍ 10:37 ያንን ከእርሱ በፊት ያለውን (መጽሃፍ) የሚያረጋግጥና በመጽሃፉ ውስጥ ያለውን የሚዘረዝር በእርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲኾን ከአለማት ጌታ (የተወረደ) ነው።
ቁርአን /ምእራፍ 10:94 ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትኾን እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ ,,,
ቁርአን /ምእራፍ 16፡123 ከዚያም ወደ አንተ የኢብራሂምን ሃይማኖት ቀጥተኛ ሲሆን ተከተል,,,

(እንዲሁም ቁርአን /ምእራፍ 27፡76፣ 4፡136 2፡285 43፡43-45 6፡89-90 42፡15 ንብቡ።)

ከላይ በተጠቀሱት የቁርአን ጥቅሶች መሰረት የመሐመድ መልእክትና ተግባር ከእርሱ በፊት ከነበሩት ነብያት ጋር የተጣጣመ መሆን አለበት። መሐመድም ተከታዮቹ የእሱን ምሳሌ እንዲከተሉ አስተምሮአል። መሐመድ ጥሩ ስነምግባር ነበረውን?

ቁርአን /ምእራፍ 3፡31 በላቸው፦ አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና,,,
ቁርአን /ምእራፍ 33፡21 ለናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለኾነ ሰው አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልክተኛ መልካም መከተል አላችሁ።

እውነተኛ ነቢያት በመጽሃፍ ቅዱስ ውሰጥ መስረቅን፣ ማታለልን፣ ምንዝርናንና ባእድ አምልኮን ተቃውመዋል ክደዋልም። እናም መሐመድ የእነዚህን ቀደምት ነብያት ፈለግ ተከትሎአልን? ትምህርቱና ተግባሩስ መጽሃፍ ቅዱስን ያረጋግጣልን? እስኪ ይህ እውነት እንደሆነ እንመልከት።

ሀ) መሐመድና የጣኦት አምልኮ 
ዘፀአት 20:4-5 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኋ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውን ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው አታምልካቸውም ,,,

(እንዲሁም 1ኛ ነገስት 19፡18፣ 2ኛ ነገስት 18፡1-4)

እነዚህ ከላይ የዘረዘርናቸው ጥቅሶች የሚያሳዩት ማናቸውንም አይነት ምልክትና ቅርጽ መሳም፣ ለእነርሱም መስገድ ወይም እጣን በማጨስ ሀይማኖታዊ ውዳሴን ማቅረብ እንደማይቻል ነው። ከታች በተጻፈው ሃዲት ግን መሐመድ ለግኡዝ አካል ሐይማኖታዊ የአምልኮ ተግባር እንደፈፀመ ያስረዳናል።

ሳሊም እንደተረከው አባቱ እንዲህ አለ፥ የአላህ መልክተኛ ወደመካ መጥቶ ተውፊድ ሲያደርግ በመጀመሪያ የጥቁሩን ድንጋይ ጠርዝ ከሳመ በኋላ ከሰባቱ ዙር ሶስቱን ዙሮች ራማ አደረገ።  (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 2 መጽሃፍ 26 ቁጥር 673) (እንዲሁም ቁጥር 675፣ 676፣ 679፣ ና 680)

አቢስ ቢን ራቢያ እንደተረከው፦ ኡመር ወደ ጥቁሩ ድንጋይ ቀረብ ብሎ ድንጋዩን በመሳም እንዲህ አለ፥ “አንተ ድንጋይ እንደሆንክ ማንንም ልትጎዳ ወይም ልትጠቅም እንደማትችል ምንም ጥርጥር የለኝም። የአላህ መልክተኛ ሲስምህ ባላይ ኖሮ ባልሳምኩህ ነበር።” (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 2 መጽሃፍ 26 ቁጥር 667)

የመሐመድ ተከታይ የሆነው ኡመር መሐመድ ሲስመው ባያይ ኖሮ ጥቁሩን ድንጋይ እንደማይስመው ይልቁንም ድንጋይ ስለሆነ እንደማይጎዳ እንኳን ሲናገር፣ ይህ ማስተዋል ግን ከመሐመድ ርቆ ነበር። መሐመድ እንደቀደሙት ነብያት አንዱን እግዝአብሄርን የሚያመልክ ቢሆን ኖሮ ለምን ለጣኦት ሰገደ? ለምን ጥቁሩን ድንጋይ ሳመ? እንዲሁም ተከታዮቹ የእሱን ምሳሌ እንዲከተሉ ለምን አስተማረ?

ለ) መሐመድ ሃሰትን አስተምሮአል
ከአስርቱ ትእዛዛት መካከል አንዱ አትዋሽ የሚል ሲሆን (ዘለዋውያን 19፡11-12 ዘፀአት 20፡16፣ ማቴዎስ 19፡18) በመሐመድ ትምህርት የምንመለከተው ግን ተቃራኒውን ነው። ቁርአን ሙስሊሞች እውነተኛ እምነታቸው በልባቸው ውስጥ እስካልተናወጠ ድረስ ሙስሊም ካልሆኑት ጋር ሲኖሩ ከእነዚህ ሰዎች ሊደርስባቸው ያለውን ጉዳት ለማስቀረት ሲሉ ስለእምነታቸው ሊዋሹ እንደሚችሉ ያስተምራል። (ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 16፡106)
የሃይማኖትን ስደት ለማስቀረት ሲባል መዋሸት ይጠበቅባቸዋልን? ሊደርስባቸው ካለው መከራ አምላካቸው ሊያድናቸው አይችልምን? ባያድናቸውስ ለአምላካቸው ታማኝ መሆን የለባቸውምን? መሐመድ ለአምላካቸው እስከሞት ድረስ የታመኑትን ወጣቶች የሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብድናጎንን ታሪክ አያውቅምን? እነዚህ ወጣቶች መከራ በደረሰባቸው ጊዜ ስለእምነታቸው መዋሸት አላስፈለጋቸውም ነበር። እንዲያውም የታመኑት አምላካቸው ከሚነደው እሳት አድኗቸዋል። (ዳንኤል 3፡16-18 ና 27)
መሐመድ ተከታዮቹ እንዲዋሹ መፍቀድ ብቻ ሳይሆን አምላክንም ሃሰተኛ ነው ሲል ይከሰዋል። እንደ መሐመድ አባባል አምላክ በጣም ጥሩ አታላይና ከፋፋይ ነው (ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 4፡142፣ 3፡54 8፡30)። በቁርአኑ ውስጥ አላህ ሙስሊሞች እውነቱን ቢያሳያቸው ስለሚፈሩ ለእሱ ብለው እንዲዋጉ ሲል ማታለልን ተጠቅሞ ነበር። ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 8፡43 እንዲህ ይላል፥ “አላህ በህልምህ እነሱን ጥቂት አድርጎ ባሳየህ ጊዜ (አስታውስ) እነሱን ብዙ አድርጎ ባሳየህ ኖሮ በፈራችሁና፥ በነገሩ በተጨቃጨቃችሁ ነበር። ,,,” ለምን እውነቱን አሳይቶአቸው የእርሱ የጉልበቱና የኃይሉ ብርታት ከጠላቶቻቸው የበለጠ እንደሆነ ሊነግራችው አልቻለም? የሚተማመኑት በአምላካቸው ሳይሆን በራሳቸው ኃይል ነውን?

በተቃራኒው መጽሃፍ ቅዱስ እግዚአብሄር ባህሪው ስላልሆነ ሊዋሽ እንደማይችል ይናገራል። ውሸት ቁርኝነቱ ከድያብሎስ ጋር ነው (ዕብራውያን 6፡18፣ ሁልቁ 23፡19፣ ዮሐንስ ወንጌል 8፡44)። የሶርያ መንግስት ከእስራኤል ጋር ጦርነት በገጠመ ጊዜ የእግዚአብሄርን አገልጋይ ኤልሳዕንና ረዳቱን ሰላዮች ናቸው በሚል ሰበብ ሊገድላቸው ጦር በሰደደ ጊዜ የኤልሳዕ ረዳት በጣም ፈርቶ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሄር ትንሹን ትልቅ አድርጎ በማሳየት አልዋሻቸውም። “የእግዚአብሄር ሰው ሎሌ ማለዳ ተነስቶ በወጣ ጊዜ፥ እንሆ፥ በከተማይቱ ዙሪያ ጭፍራና ፈረሶች ሰረገሎችም ነበሩ። ሎሌውም፦ ጌታዪ ሆይ፥ ወዮ! ምን እናደርጋለን? አለው። እርሱም፦ ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ አለው። ኤልሳዕም፦ አቤቱ፥ ያይ ዘንድ አይኖቹን እባክህ ግለጽ ብሎ ጸለየ። እግዚአብሄርም የብላቴናውን ዓይኖች ገለጠ፥ አየም፤ እነሆም፥ በኤልሳዕ ዙሪያ ያሉት የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች ተራራውን ሞልተውት ነበር።” 2ኛ ነገስት 6፡15-17   
መሐመድ ውሸት ይፈቀዳል ብሎ ማስተማሩ ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚዎቹንም ለመግደል ውሸትን ተጠቅሞአል።
ጃቢር ቢን አብዱላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አለ፥ “አላህንና የአላህን መልክተኛ የጎዳውን ካብ ቢን አል-አሽራፍ ማነው የሚገድልልኝ?” መሐመድ ቢን ማስላማ ተነስቶ፥ “ኦ የአላህ መልክተኛ! እንድገድለው ትፈልጋለህን?” ነብዩም፥ “አዎ።” መሐመድ ቢን ማስላማም፥ “እንግዳው እንድዋሸው (ካአብን ለማታለል) ፍቀድልኝ።” ነብዩም ትችላለህ ተናገር አለው። ,,, (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 5 መጽሃፍ 59 ቁጥር 369) (እንዲሁም ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 4 ፍ 52 ቁጥር 270 ና 271)

 ,,, ኢብን ሽሃብ እንዳለው ውሸት በሶስት ጉዳዮች ተፈቅዶአል፦ በጦርነት ጊዜ፣ በሰዎች መካከል እርቅ ለማድረግ፣ ባል ከሚስቱ እንዲሁም ሚስት ከባልዋ (ለማስታረቅ ሲባል) ጋር ሲነጋገሩ መዋሸት ይችላሉ። (ሳሂህ ሙስሊም መጸሀፍ 032 ቁጥር 6303-05) (እንዲሁም ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 3 መጽሃፍ 49 ቁጥር 857)
ባልና ሚስት እርስበርሳቸው እውነትን ካልተነጋገሩ ምን አይነት ትዳር ነው? እግዚአብሄር በኤፌሶን 4:25 ላይ “ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ” ይለናል።
መሐመድ የአምላክን ትእዛዝ ተላልፎአል፣ ተከታዮቹንም እንዲሁ እንዲያደርጉ አዞአል፣ እንዲሁም አምላክን ሃሰተኛ ብሎታል። እንደመጽሃፍ ቅዱስ ከሆነ አታላይና ሃሰተኛ ዲያብሎስ ነው።

ሐ) መሐመድ ዝሙትን ፈጽሞአል
እግዚአብሄር በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ የሌላውን ሚስት መመኘትን አውግዟአል (ዘፀአት 20፡17፣ ዘዳግም 5፡21፣ ማቴዎስ 5፡27-28)። ቁርአን ግን አላህ መሐመድን የሌላውን ሰው ሚስት እንዲፈልግ አነሳስቶታል ይለናል። ይህም መሐመድ እንዲያገባት ሲል ያሳደገው ልጁ ሚስቱን እንዲፈታ አድርጎታል። ይሄንንም ክፉ ኃጥያት እንዲፈጽም አላህ ለመሐመድ ያዘዘበትን ምክንያት ሲናገር አባቶች የአሳደጉአቸውን ልጆች ሚስቶችን ማግባት እንደሚችሉ መሐመድ ምሳሌ እንዲሆን ነው ይለናል (ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 33፡37)።
ትምህርት ለመስጠት በሚል ሰበብ መሐመድ የተመኛትን ሴት ለማግባት ሰው ሚስቱን እንዲፈታ ማድረጉን መቀበል በጣም የሚከብድ ነገር ነው።
መሐመድ ለራሱና ለተከታዮቹ የጦር ምርኰኛ ከሆኑ ሴቶች ጋር ከጋብቻ ውጭ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት እንዲያደርጉ ፈቅዶአል። 

እግዚአብሄር ለእስራኤላውያኖች በጦር ከማረኩአቸው ሴቶች መካከል ማግባት እንደሚችሉ ነገር ግን ሊሸጡአቸው ወይም ሊጫወቱባቸው እንደማይችሉ ተናግሮአቸዋል። እነዚህን ሊያገቡአችው የሚፈልጉትን ምርኮኞች ለ 30 ቀናት ያህል የቤተሰባቸውን ሃዘን እስኪወጡ ድረስ መጠበቅ አለባቸው። ይህም ሴቲቷን ሊያገባት በፈለጋት ሰው እንዳትደፈርና ከእርሱና ከሌሎች እስራአላውያን ጋር ለመቀላቀል እንዲያግዛታ ነው (ዘዳግም 21፡10-14)።

መሐመድ ግን በተቃራኒው ተከታዮቹ በእጆቻቸው ከወደቁት ምርኰኞች እና ባሪያዎች ጋር ከጋብቻ ውጭ ግንኙነት እንዲያደርጉ ፈቅዶላቸዋል (ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 4:24፣ 23፡5-6 33፡50 70፡29-30)።

መሐመሁለት ቅምጦች ነበሩት የመጀመሪያዋ የኮፕቲኳ ማሪያ ቢንቱ ኡም ኢብራሂም ሌክሳንደሪያና የግብጽ ወታደራዊ ዛዥ ከሆነው -ሙቃውቂ ስጦታ ስትሆን,,, ሁለተኛዋን ቅምጥ በተመለከተ ሪሐናቢንቱ ምሩ ወይም ቢንቱ ዘይድ የተባለችው ከባኒ ኳራዲሀ ምርኮኞች መካከል የመረጣት ት,,, (የነብዩ መሐመድ ራህ/ህይወት ታሪክ (The Seerah of Prophet Muhammad (S.A.W.))፣ በመሐመድ አሊ አል ሃላቢ አል አታሃሪ በአጭሩ የተዘጋጀ፣ አል ፊርዶስ ኤል ቲ ዲ፣ ሎንደን፣ የመጀመሪያ እትም 2001፣ ክፍል 2 ገጽ 32-33)

ብዱል ዚዝ እንደተረከው፦ አስ እዲህ አለ፥ “ላህ መልክተኛ ካሃበርን እንደወረረ,,, አሸንፎ ምርኮኞችንና ምርኮን ሰበሰብን ዲሀያም ወደ ላህ መልክተኛ መጣና ኦ የአላህ መልክተኛ! ከምርኮኛ ልጃገረዶች ባሪያ ሥጠኝ ብሎ ጠየቀ ነብዩ ሂድና ንዷን ውሰ ለው ርሱም ሳፊያ ቢንት ሁያይን ወሰደ ንድ ሰው ወደ ነብዩ መጥቶ ላህ መልክተኛ! ሳፊያ ቢንት ሁያይን ሃያ ሰጠኸው ርሷ የኳራይዛና ናዲር ጎሣ ዥ ለሆነው ባለሟል ነበረ ንተ ንጂ ለሌላ ትሆንም ለው ከዚያ በኋላ ነብዩ ቱንም ምጡልኝ ብሎ ዘዘ ዲሃያም ከሴትየዋ ጋር በመጣ ጊዜ ነብዩ ያትና ለዲሃያ ንዲህ ለው የፈለከውን ልጃገረድ ርሷ ውጭ ውሰድ ለው።” ,,,  (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 1 መጽሃፍ 8 ቁጥር 367)

ጃቢር ንደዘገበው ንድ ሰው ወደ ላህ መልክተኛ (ሠላም ርሱ ላይ ይሁን) መጣና ንዲህ ንዲት ባሪያ ለችኝ የቤቴ ገልጋይ ነች ውሃ ትቀዳልናለች ናም ርሷ ጋር ግንኙነት ደረግሁ ንድታረግዝ ግን ልፈልግምላህ መልክተኛ ንዲህ ለው ከፈለግህ ዚል ድርግ ግን ርሷ የተወሰነው ይሆናል ሠውየውም ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ተመልሶ መጣና ንዲህ ልጅቱ ረገዘች ርሷ የተወሰነው ይሆናል ብየህ የለም ለው( ሙስሊም መጽሐፍ 008 ቁጥር 3383)

አል ኩድሪ ንደዘገበው በሃናይን ውጊያ ጊዜ ላህ መልክተኛ (ሠላም ርሱ ላይ ይሁን) የጠላትን ጦር ንዲዋጋ ጦር ወደ ውታ ላከ ድል ድርገው ምርኮኛ በወሰዱ ጊዜ ላህ መልክተኛ (ሠላም ርሱ ላይ ይሁን) ጃቢዎች ባሎቻቸው ምላኪ በመሆናቸው ከምርኮኛ ሴቶች ጋር በግብረ ስጋ መገናኘት ከብዶአቸው ነበር። ከዚያም እጅግ ከፍ ያለው ላህ በዚህ ጉዳይ ላይ መልክት ላከ ንዲህ ሲል ,,, ጅህይ የወደቀች ሴት ለመገናኘት ትችላለህ (424),,, (ሳሂህ ሙስሊም መጸሐፍ 008 ቁጥር 3432) (እንዲሁም ሳሂህ ሙስሊም መጽሐፍ 008 ቁጥር 3371)

ስለዚህ ስልምና አምላክ መልክተኛው የጎረቤቱን ሚስት ንዲመኝ ፈቅዶለታል (በተለይም ያሳደገውን የልጁን ሚስት) በልቡም ዝሙት አስፈጽሞታል፣ እንዲሁም የልጁን ሚስት አስፈትቶ አጋብቶታል። ከዚህም በተጨማሪ ላህ መሐመድንና ተከታኞቹን በባርነትና በምርኮኝነት ከያዟቸው ያገቡ ሴቶች ጋር ዝሙት ንዲፈፅሙ ፈቅዶላቸዋል ታዲያ የስጋ ምኞቱን ለማካት ግዚብሔርን ሕግ የጣሰውን መሐመድ ግዚብሔር ነብይ ነው ንዴት ንላለን?

) ዝሙት በገነት
በመጽሐፍ ቅዱስ (ሉቃ 20፡34-36) ጌታችን የሱስ ክርስቶስ ሰዎች በመንግስተ ሰማይ/በገነት ያገቡምይጋቡም ንደ መላእክ ናቸውና ብሎ ተናግሯል ሐዋሪያው ጳውሎስም በሮሜ 14፡17ግዚብሔር መንግስት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ደስታ ናት ንጂ መብልና መጠጥ ይደለችምብሏል ርአ ግን በተቃራኒው ገነት ለሚገቡ መልካ ሰዎች የተዘጋጁ ድንግልናቸው በሌላ ወንድ ያልተገሰሰ፣ ዓይነ ትልልቅ የሆኑ፣ ነጫጭ ቆንጆዎች፣ የተሸፈነ ሉል የሚመስሉና ጅግ በጣም የሚያማልሉ ሴቶች ንደተዘጋጁ በግልጽ ይናገራል

ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 44፡54 (ነገሩ) ንደዚ ነው ይናሞች የሆኑ ነጫጭ ሴቶችንም ናጠናዳቸዋለን
ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 52፡20 በተደረደሩ ልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ሆነው (በገነት ይኖራሉ) ይናማዎች በሆኑ ነጫጭ ሴቶችም ናጠናዳቸዋለን
ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 55፡56 በውስጣቸው ከበፊታቸው (ከባሎቻቸው በፊት) ሰውም ጅንም ያልገሠሣቸው አይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች (ሴቶች) አሉ። 70 በውስጣቸው ጠባየ መልካሞች መልከ ውቦች (ሴቶች) 72 በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የሆኑ ናቸው 74 ከነሱ በፊት ሰውም ንም ልገሰሳቸውም
ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 56፡22-24 ይናማዎች የሆኑ ነጫጭ ቆንጆዎች ሏቸው ልክንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የሆኑ በዚያ ይሰሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይሆን ዘንድ (ይህንን ደረግንላቸው)።
ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 78፡31-33 ለጥንቁቆች መዳኛ ስፍራ ላቸው ትክልቶችና ወይኖችም ኩያዎች የሆነ ጡተ ጉቻማዎችም

አቡ ሁሬይራ እንደተረከው ላህ መልክተኛ እንዲህ አ፥ “የመጀመሪያዎቹ (ሰዎች) ወደገነት ቡት ,,,  ሁለት  ሚስቶች ከአይናማዎች መካከል ይኖራቸዋል (ቆነጃጅቶች፣ ንጹህና ሰውነታቸው የሚያንጸባርቅ፣ አጥንታቸውና ስጋቸውን አልፎ የእግሮቻቸው አጥንት መቅኔ የሚታይ)።(ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 4 መጽሃፍ 54 ቁጥር 476) (እንዲሁም ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 4 መጽሃፍ 54 ቁጥር 469 ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 4 መጽሃፍ 55 ቁጥር 544፤ ሂህ ሙስሊም መጽሃፍ 040 ቁጥር 6793 ቁጥር 6795 እና ቁጥር 6798)

አብዱላህ ቢን ቋስ እንደተረከው፦ ላህ መልክተኛ እንዲህ አ"በገነት 60 ማይል ስፋት ያለው ከዕንቁ በተሰራ ህንጻ ውስጥ በየ ጥጉ ላይ የሚቆሙ ሴቶች በሌላው ጥግ ካሉ ጋር የማይተያዩ ይኖራሉ፤ አማኞች ይጎበኙአቸዋል ይደሰቱባቸዋል ,,, " (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 6 ፍ 60 ቁጥር 402)

ያለውን አናስ እንደተረከው፦ በገነት የሚኖሩማኞች ሁሉ የግብረ ሥጋን ግኑኝነት መፈጸም የሚያስችላቸው ልዩ የሆነ ኃይል ላህ ይሰጣቸዋልእሱም ተጠየቀላህ መልክተኛ ሆይ! ሰው እርግጥ ግብረ ሥጋ ግኑኝነት መፈጸም ይችላል ማለት ነውን?ነቢዩም ሲመልወደ ገነት ለገባ ሰው ይህንን ለማድረግ የሚያስችለው ንዱ ሰው የመቶ ሰው ጉልበት ይሰጠዋል አለ።(አል-ቲርሚዲህ ቁጥር 2459)

ንግዲህ ንደ መሐመድ ባባልና ምህርት ከሆነ በዓለም ላይ ስንኖር የምናገኛቸው ሥጋዊ የሆኑ ደስታዎችና ዓለማዊ ስተሳሰቦች በገነት ማለት ነው መሐመድ አላህ ማኞቀኑን ሙሉ ቆመው የሚጠብቁ ልጃገረዶችን በገነት ንዳዘጋጀና ተከታዮቹም ከእነዚህ ልጃገረዶች ሥጋዊ/ወሲባዊ ደስታንደሚያገኙ ረጋ ይለናል። ይህ ደግሞ ልዩ በሆነው ግዚብሔር መገኛና ሰዎች ከክርስቶስ ጋር ያላቸው ልዩ የሆነንድነትና ፍቅር በሚገለጽበት ሥፍራ ሥጋዊና ዓለማዊ ቶች በሙላት ይገለጻሉ ማለት ነው መሐመድ ወረደልኝ ያለው ቁርዓንና የመሐመድ ተገባሮችና ንግግሮች የተጻፉበት ሃዲ የሚሰጡን የገነት/መንግስተ ሰማይ በጣም የሚያደነግጥ በኃጢዓት የተሞላ ሥፍራ ነው

ላህ ሰብዓዊ ፍጡርን/ልጃገረዶችን ለወሲባዊ ርካታ ብቻ ለዘላለም ባርያ እንዲሆኑ ፈጥሯል መባሉ ያስደንቅም? ይህ በቁርዓንና በመሐመድ ስተምህሮ የተገለጸው ገነት የሰውን ኃጢዓተኛና ሥጋዊ ባህሪ ቁልጭ ድርጎ ያሳየናል ከዚህ ሁሉ ሥጋዊና ሥነ ምግባር ከጎደለው ባህሪውና ትምህርቶቹ ጋር ንዴት ድርገን መሐመድን ነቢይ ነው ልንለው ንችላለን?

ሠ) ተቃዋቹን መግደሉና መበቀሉ
መጽሐፍ ቅዱስ ማኞችም ሆኑ ነቢያቶች በኃይል ሌሎች እንዲቀበሉአቸው ፈጽመው ጦር እንዳያነሱ በሀማኖታቸው ምክንያት ለተነሳባቸው ተቃውሞ መበቀልም እንኳን እንደሌለባቸው በግልጽ ያስተምራል። ለእነሱ የሚዋጋላቸው፣ የሚከላከልላቸውና የሚበቀልላቸው ምላክ ስላላቸው ራሳቸው የበቀል ርምጃ ንዳይወስዱ ያስጠነቅቃቸዋል (ዘሌዋ 19፡18 ማቴዎስ 5፡39 ና 44 ማቴዎ 26፡52 ማቴዎ 22፡39-40 ኤፌሶ 6፡12 ዕብ 10፡30)።

ዕብራ 10፣30 በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ ያለውን እናውቃለንና፤ ደግሞም ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል።

በተቃራኒው ደግሞ ቁርአን ለፈጣሪና ለሃይማኖት መዋጋት ተቀባይነት ያለው ነገር ነው ብሎ ያስተምራል።

ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 4:74 እነዚያም ቅርቧን ሕይወት በመጨረሻይቱ ሕይወት የሚለውጡ በአላህ መንገድ ይጋደሉ አላህም መንገድ የሚጋደል የሚገደልም ወይም የሚያሸንፍ ታላቅ ምንዳን በእርግጥ እንሰጠዋለን
ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 4:89 (እነሱ) እንደ ካዱ ብትክዱና እኩል ብትሆኑ ተመኙ! በአላህም ኃይማኖት እስከሚሰደዱ ድረስ ከነሱ ወዳጆችን አትያዙ (ከእምነት) ቢያፈገፍጉም ያዙዋቸው (ማርኩዋቸው) ባገኛችሁበትም ስፍራ ግደሏቸው ከነሱም ወዳጅንና ረዳትን አትያዙ
ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 5፡51 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ፤ ከፊላቸው ለከፊ ረዳቶች ናቸው ከናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከነርሱ ነው፤ አላህ አመጠኞችን ህዝቦች አያቀናም
ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 8:39 እውከትም እስከማትገኝ ሃይማኖትም ሁሉ ለአላህ እስከሚሆን ድረስ ተጋደሏቸው፤ ,,,
ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 9:73 አንተ ነቢዩ ሆይ ከሓዲዎችንና መናፍቃንን ታገል፤ በነሱም ላይ ጨክን፤ መኖሪያቸውም ገሃነም ናት፤ መመለሻይቱም ከፋች

በተጨማሪም በሱራ/ምእራፍ 2፡190-191 ና 193፣ 2፡216፣ 4፡95፣ 8፡12፣ 8፡65፣ 9፡5፣ 9፡14፣ 9፡29፣ 47፡4፣ 48፡29፣ 59፡24-5፣ 61፡4 66፡9 ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ቁርዓን እስልምናን የማይከተሉትንና የሌሎች እምነት ተከታይ የሆኑትን እንዲገድሉ ያዛል

ን ኡማር እንደተረከው፦ ላህ መልክተኛ እንዲህ አ“ሰዎች አላህ ብቻ አምክ ነው መሐመድም መልእክተኛው ነው ብለው እስኪያውጁ ድረስ ወደ አላህ እስኪጸልዩ፣ የሃይማኖትን ምጽዋእት እስከሚያወጡ ድረስ እንዋጋቸው አላህ አዞኛል እንዲህ ካደረጉ ህይወታቸውንና ንብረታቸውን ከእኔ ያድናሉ ከዚያም የእስልምና ህግ መጠበቃቸው ከአላህ የያገኙት ይሆናል።(ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 1 መጽሃፍ 2 ቁጥር 25) (እንዲሁም ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 1 መጽሃፍ 8 ቁጥር 387፤ ሳሂህ ሙስሊም መጽሃፍ 001 ቁጥር 0029 ቁጥር 0030 ቁጥር 0032 ቁጥር 0033)

ን ኡመር አንደተረከው፦ ,,, የአላህ መልዕክተኛ ካይባሪን ሲቆጣጠ ምድር የአላህ፣ የመልእክተኛውና የሙስሊሞች ንብረት በመሆኑ አይሁዶችን ከዚያ ለማስወጣ አስቦ ነበር የአላህ መልክተኛ ይሁዶችን ከምድሩ ፈ ለማስወጣት በፈለገ ጊዜ ይሁዶች እዳያባቸው እሱ ለመገዛና ከሚያመርቱት ምርት ግማሽ ያህሉን ለአላህ መልክተኛና ለሙስሊሞች እናካፍላለን ሲሉ ጠየቁት። የአላህ መልክተኛም እንዲህ አላቸው “በዚህ ቅድመ ሁኔታ እስከኖራችሁና እስከፈቀድንላችሁ ድረስ ብቻ እዚህ ልትቆዩ ትችላላችሁ” ከዚያም ኡመር ወደ ታይማ እና አሪሃ እስካባረራቸጊዜ ድረስ እዚያ ቆዩ (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 3 መጽሃፍ 39 ቁጥር 531)

ኡመር ቢ አል ኪ እንደተረከው፦ የአላህ መልዕክተኛ (በእ ላይ የአላህ ሰላም ይሁን) እንዲህ አለ፥ “ክርስቲያኖችንና አይሁዶችን ከአረብ ግዛት ሁሉ አስወጣቸዋለሁ፤ ከእስላሞች በስተቀር ማንም አይኖርበትም(ሂህ ሙስሊም መጽሃፍ 019 ቁጥር 4366)

ከመሐመድ በስተቀር የትኛውም ነቢይ ኃይል በመጠቀም ሰዎችን ለመለወጥ ወይም ለማሳመን አልሞከረም የእግዚአብሔር ነቢያት ተቃውሞ ሲገጥማቸው የገጠማቸውን ነገር ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር ይናገራሉ ወይም በገጠማቸው ነገር ውስጥ ተፈትነው ያልፋሉ እንጂ ሰዎችን የሚበቀሉ የእግዚአብሔር ነቢያት እንዳሉ መጽሐፍ ቅዱስ አይነግረንም

በኦሪት ዘኀልቁ ምዕራፍ 12 ላይ የሙሴ ወንድምና እህት ሙሴን ፈጽመው ሲቃወሙት በኦሪት ዘኀልቁ ምዕራፍ 14 ላይ ደግሞ እስራኤላዊያን በሙሴና በአሮን ላይ አመጽ እንዳነ መጽሐፍ ቅዱስ ያስነብበናል በሁለቱም ቦታ ሙሴ ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱ ለ ሲሟገት እንመለከታለን በዘኁልቁ 16 ላይ ደግሞ ሙሴ የደረሰበትን ተቃውሞ ለእግዚአብሔር ሲያቀርብ በተቃዋሚዎ ላይ የራሱን ቃል ከመናገር ሲቆጠብ እናያለን ይህም የሚያሳየው ሙሴ የሚያገለግለውን አምላክ ጠንቅቆ ያወቀና አምላኩ ደግሞ የሚሰማና የሚፈርድ እንደሆነ ነው (ዘኀልቁ 16፡1-35)።

ከላይ ባየነው ታሪክ እንደተመለከትነው ሙሴ ከሌሎች ተቃውሞ ሲደርስበት ወደ አምላኩ በጾሎት ከማቅረብ በቀር አልተዋጋቸውምንም ለመበቀልና ለመግደል ሲሞክርም አናይም ማን እንደጠራውና ማንን እንደሚያገለግል ስለሚያውቅ ይጨነቅ የነበረው ለተቃዋሚዎ እንጂ ለራሱ ሥልጣን አልነበረም እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ የሚሟገት ሕያው አምላክ ነው በሌላ መንገድ ደግሞ መሐመድ ነቢይነቱን ለማረጋገጥ እሱን የተቃወሙትን ሁሉ ሲቀጣቸውና ሲገድላቸው እናያለን መሐመእውነተኛ የእግዚአብሔር ነቢይ ከሆነ እሱን የጠራው አምልክ ለሙሴና ለሌሎ ነቢያት እንዳደረገው ለምን ሊዋጋለት አልቻለም?

የብሉይ ኪዳን ነቢያት ሁሉ (የእግዚአብሔር የሆኑት) በልዩ ልዩ ተቃውሞ፣ በስደትና እንዲያውም በሞት ውስጥ አልፈዋል ስለ ራሱ ለመዋጋትና ራሱን ለመከላከል የሞከረ የእግዚአብሔር ነቢይ የለም በተቃራኒው መሐመድ ግን በሱ ላይ የሚመጣ የትኛውንም ተቃውሞና ፈተና ለመቀበል አልፈቀደም። ይልቁንም አምላኩን ወክሎ የአምላኩንና የራሱን ተቃዋሚዎች ለመበቀል አምላኩ እንዳዘዘው ይናገራል። ለመሆኑ፥ አምላኩ ስለመሐመድ ለመከራከርና ለመሟገት ኋይልና አቅም የለውምን?

ጃቢር ቢን አብዱላህ እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አለ፥ “አላህንና የአላህን መልክተኛ የጎዳውን ካብ ቢን አል-አሽራፍ ማንነው የሚገድልልኝ?” መሐመድ ቢን ማስላማ ተነስቶ እንዲህ አለ፥ “ኦ የአላህ መልክተኛ! እኔ እንድገድለው ትፈልጋለህን?” ነብዩም እንዲህ አለ፥ “አዎ” መሐመድ ቢን ማስላማም፥ “እንግዳው እንድዋሸው (ካአብን ለማታለል) ፍቀድልኝ።” ነብዩም ትችላለህ ተናገር አለው። ,,, (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 5 መጽሃፍ 59 ቁጥር 369)

ከመዲናውያን ወገን የሆነችና ምንም ሃይማኖት ከሌላቸው ሰዎች መካከል የሆነች  አስማ የምትባል ገጣሚ ሴት ነበረች የባለቤቷም ስም  ያዚድ ቢ ዛይድ ይባል ነበር። ይህቺ ሴት የመዲናን ሰዎች እንግዳውን መሐመድን በመታዘዛቸውና በመቀበላቸው እንዲሁም በህዝቡ ላይ ያሳደረውን ጫና በመቃወም ባለመዋጋታቸው በግጥሟ ኮነነቻቸው መሐመይህቺ ሴት ምን እንዳለች በሰማ ጊዜ፣ “የማራዋን ልጅ ማን ያግድል?” ሲል ጠየቀ በዚያው ምሽት የባሏ ወገን የሆኑ ሰዎች ሌሎች የነቢዩ ተከታዮች ወደዚያች ሴት ቤት በድብቅ ገቡ። ሴትየዋ አምስት ልጆች ነበሯት፣ የመጨረሻው ልጁዋ ጡቷን እንደያዘ ደረቷ ላይ ተኝቶ ነበር ከገዳዮቹ አንዱ ቀስ ብሎ ልጇን ከጡቷ ላይ ካላቀቀ በኃላ ሰይፉን በመምዘዝ በተኛችበት ወ ገደላት። ው ቀን ማንም ይህንን አሰቃቂ ወንጀል እንዳይበቀል የነቢዩ ሰዎች በተቻለ መጠን እርምጃ መውሰድ ጀመሩ የነቢዩን ድርጊት ማንም ቢሆን መቃወም አልቻለም ነበር ሌላው ቀርቶ የገዛ ባሏ እንኳን የነቢዩን ድርጊት መቃወም አልቻለም። (ኢብን እሻቅ፣ የመሐመድ ህይወት ታሪክ (The Life of Muhammad)፣ በ ኤ ጉላኡም የተተረጎመ፣ ኦክስፎርድ ዩፒ፣ 1955፣ 2004፣  ገጽ 675-676)

አቡ ኡፋክ የሚባ ከአንድ መቶ አመታት በላይ ዕድሜ ባለጸጋ ከመዲና ጎሳዎች አባል የነበረ ሰው ነበር። ህ ሰው ማናት ከምትባል አማልክት ጋር ግኑኝነት የነበረው ሲሆን መሐመድን የሚያዋርድ፣ የን ጎሳዎች ቅድመ አያቶች ንካሬነት፣ ለሌሎች የማይሸነፉ እንደነበሩ ነገር ግን መሐመድ ባመጣው ሃይማኖታዊ ትዕዛዝ የመዲና ጎሳዎች ሁለት ቦታ እንደተከፈሉ ግጥም ጽፎ ነበረ
ይህንን የሰማው መሐመድ “ይህን ሌ የሚገዳደርልኝ ማነው?” ሲል ጠየቀም ኢብን ኡማየር የሚባል ሰው በባድር ጦርነት ተካፋይ የነበረ “አቡ ኡፋክን እገድለዋለሁ ወይም እኔ ከሱ ቀድሜ እሞታለሁ” ሲል ለመሐመድ የመሃላ ቃል ገባ ከዚያም ዕድልና ጊዜ ጠብቆ ሙቀቱ እጅግ ከፍተኛ በሚሆንበት ወቅት አቡ ኡፋክ በምሽት ሜዳ ላይ ተኝቶ አገኘው ከዚያም በያዘው ሰይፍ በጉበቱ በኩል አልፎ አልጋውን እስኪነካው ድረስ ወጋው የአላህ ጠላት ብሎ ጮኸ ከገዳዩ ጋር የነበሩት ሰዎች ፈጥነው ወደ ቤቱ አስቡት። (ኢብን እሻቅ፣ ገጽ 675 እና ኢብን ሳድ፣ የዋነኛ ክፍሎች መጽሃፍ (Kitab Al Tabaqat Al Kabir/Book Of The Major Classes)፣ የእንግሊዝኛ ትርጉም በ ኤስ ሞይኑል ሃቅ M.A. PH.D ረዳት ተርጓሚ ኤች ኬ ጋሃዛንፋር M.A.፣ ኪታብ ባሃቫን አስመጭና ላኪ፣ 1784 ካላን ማሃል፣ ዳርያጋንጅ፣ ኒው ደሊህ - 110 002 ህንድ፣ ክፍል 2 ገጽ 32)
ጌታ ኢየሱስ እንደነዚህ አይነት ሰዎችን “እናንተ ከአባታችሁ ከዲያቢሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ እውነትም በእርሱ ስለሌለ በእውነት አልቆመም ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና (ዮሐንስ 8፡44) በማለት አስጠንቅቋል

እንዲህ አይነት በቀለኛና ነፍሰ ገዳይ ሰው እንዴት የአግዚአብሔር መልዕክተኛ ሊሆን ይችላል?

ረ) መሐመድ ስለደህንነቱ እርግጠኛ ያልሆነና በአምላኩ መተማመን የሌለው ሰው ነበር
ከመሐመድ በፊት የነበሩ ነቢያት በሚያገለግሉት እግዚአብሔር ላይ ፍጹም መታመን የነበራቸውና ፍጻሜያቸውንም የሚያውቁ ነበሩ ያመኑት እውነተኛ ስለሆነ የሚጠብቃቸውን ሽልማትና ክብር የሚያውቁና የማይናወጥ እምነት ነበራቸው (ዮሐንስ 6፡68-69፣ ዮሐንስ 10፡28-30፣ ዮሐንስ 11፡25-27፣ 1ኛ ዮሐንስ 4፡16፣ ሮሜ 8፡18)። ጻሜው የሚፈራ እና የሚሰጋ ሰይጣን ብቻ ነው (ማርቆስ 1፡24)።

መሐመድ ግን አገለግለዋለሁ ስለሚለው አምላክ ፍጹም የሆነ ጥርጣሬ ነበረው። የሚከተለውን ጥቅስ ከቁርአን እንመልከት።

ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 46፡9 ከመልዕክተኞች ብጤ የሌለኝ አይደለሁም በኔም በእናንተም ምን እንደሚሠራም አላውቅም፤ ወደ እኔ የሚወረደውን እንጂ ሌላን አልከተልም እኔም ግልጽ አስፈራሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም በላቸው

,,, ነቢዩ እንዲህ ብሏል,,, እኔ ምንም እንኳን የአላህ መልክተኛ ንም አላህ በእኔ ላይ ምን እንደሚያደርግኝ ገና አላወኩም የማንም መጨረሻ ምን እንደሆነ ማረጋገጥ አልችልም ያ ደግሞ ያሳዝነኛል ,,,(ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 5 58 ቁጥር 266)

መሐመድ ስለሚያመልከው አምላክ መተማመን ከሌለው እኛ እንዴት መልእክቱን ትክክለኛ ነው ብለን እንዲሁም እሱን እንደ እውነተኛ ነብይ ልንቀበል እንችላለን? ለራሱ ዋስትና የሌለው ሰው ለተከታዮቹስ የሚሰጠው ምንአይነት ዋስትና ነው?

) የስነ ምግባር ጉድለት - ሚስቹ ጋር የነበረው ሁኔታና ለሴቶች ያለው አመለካከት
የመጀመ ሚስቱ ከድጃ ከሞተች በኋላ ልጆቹን በማሳደግ እንድትረዳው በእድሜዋ ጠና ያለች ሳውዳ የምትባል ባሏ የሞተባት ሴት አግብቶ ነበር።  መሐመድም በገንዘብና በስልጣን እየበረታ በመጣ ቁጥር ወጣትና ቆነጃጅት የሆኑ ሴቶችን የራሱ የማድረግ እድል አጋጠመው። ይህም በችግሩ ጊዜ ከጎኑ የነበረችውን በኋላም እድሜዋ እየገፋና ውበቷ እየቀነሰ የመጣችውን ሳውዳን ጣል ጣል ማድረግና ይልቁንም ሊፈታትም መፈልጉ በተለያዩ ሃዲቶች ተዘግቦአል። የሚቀጥለውም የቁርአን ክፍል የወረደው ሳውዳ መሐመድ ሊፈታት በፈለገ ጊዜ ከእርሱ ጋር ትዳርዋን ለማቆየት ከተደራደረች በኋላ ነበር።

ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 4፡128 ሴትም ከባልዋ ጥላቻን ወይም ፊቱን ማዞርን ብታውቅ በመካከላቸው መስማማትን ቢስማሙ በሁለቱ ላይ ሃጥያት የለም። ,,,
በኢብን አባስ ስልጣን አት-ቲርሙዲ እንደተተረከው፦ " መሐመድ ይፈታኛል ብላ በፈራች ጊዜ ለአላህ መልእክተኛ እንዲህ አለች፥ አትፍኝ ይልቁንም ከአንተ ጋር የሚኖረኝን ቀኔን ለአይሻ እሰጣለሁ’" ም አላህ የቁርአን ክፍል አወረደ (ሱራ/ምእራፍ 4፡128)። (የተከበሩት የነብዩ ባለቤቶች (The Honorable Wives of the Prophet)፣ አራሚ አብዱል አሃድ፣ ዳሩሳላም ማተሚያና ማከፋፈያ፣ ሪያድ፣ ጂዳህ፣ ሻርጃህ፣ ላሆር፣ ሎንደን፣ ሂዩስተን፣ ኒው ዮርክ፣ የመጀመሪያ እትም ጥቅምት 2004፣ 64-65)
አይ እንደተረከችው፦ ,,, ህን መልእክተኛ ለማስደሰት ስትል ሳውዳ  ቢንት ዛማ መልእክተኛው የሚጎበኛትን ቀን ተራዋን ለአይሻ አሳልፋ ሰጠች። (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 3 መጽሃፍ 47 ቁጥር 766) (ሂህ ሙስሊም መጽሃፍ 008 ቁጥር 3451)

ለሌሎች ታላቅ ምሳሌ ሊሆን የተጠራው የአላህ መልእክተኛ የተጨነቀችና የፈራች ሚስቱን ምንም ብታረጅና ውበትዋ ቢቀንስም አይዞሽ አልፈታሽም ከአንችም ጋር የማሳልፈውን ቀን ለማንም አልሰጥም ብሎ ሊያጽናናት አይገባምን? በችግሩ ጊዜ አብራ የተቸገረችውን ዝናንና ስልጣንን እንዲሁም ወጣትና ቆነጃጅት ሚስቶችን ባገኘ ጊዜ እንዳረጀች እቃ መቁጠር ይህ ምን አይነት ስነምግባር ነው?
 
በአንድ ወቅት ደግሞ ኡሙ ሰላማ የተባለችው የመሐመድ ሚስት ለአይሻ በሚያሳየው ቀረቤታ ተከታዮቹ መሐመድ አይሻን የሚጎበኝበትን ቀን በመጠበቅ ስጦታ በማምጣታቸው የተቀሩት ሚስቶቹን ወክላ ተቃውሞ አቀረበች። የመሐመድም መልስ "ክሽን በአይሻ አታስቸግሪኝ፤ የአምላክ ቃል የሚመጣልኝ ከማናችሁም ይልቅ በእርስዋ አልጋ ውስጥ ብቻ ስሆን ነው” (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 3 መጽሃፍ 47 ቁጥር 755) የሚል ነበር። መሐመድ ከሌሎቹ ሚስቶቹ ይልቅ ለአይሻ የሚያደርገውን አድልዎ ለመሸፈን ሲል ቁርአኑ ከአላህ የሚወርድልኝ በአይሻ አንሶላ ውስጥ ብቻ ነው ብሎ ማሳበቡ ድንቅ ነገር ነው።

ሌላው  አላህ ለመሐመድ አድልዎ ሲያደርግ ለእሱ የፈለገውን ቁጥር ያህል ሚስቶች እንዲያገባ ሲፈቅድለት (ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 33፡50) ይኸውም አላህ የራሱን እስከ አራት ሚስቶች (ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 4፡3) የሚለውን ትእዛዝ ለመጣስ መገደዱን ማየት አስገራሚ ነገር ነው። በተለይም አላህ ለተከታዮቹ አራት ሚስቶችን ለማግባት ሚስቶቹን በእኩልነት ማስተዳደር የሚችል ብሎ ያቀረበውን ቅድመ ሁኔታ መሐመድ አለመጠበቁና ለእራሱም ድክመት ማካካሻ እንዲሆን በባሎቻቸው የተጣሉ ሚስቶች ባሎቻቸው እንዳይፈቷቸው ሲሉ የተወሰኑ የጋብቻ መብታቸውን ሊተው ይችላሉ ብሎ (ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 4፡128 እና 129) ሌላ የቁርአን ክፍል ማውረዱ የአሁኑ ባሰ ያሰኛል።

መሐመድ ሚስቶች ለባሎቻቸው ባይታዘዙ አ ድብደባ በእነሱ ላይ እንዲፈጸም ሲያውጅ ይህንንም የፈጸሙ ባሎች ምክንያታቸው ምን እንደሆነ ሊጠየቁ አይገባም ሲል አሳስቦአል።

ኡመር ኢብን አል-ኪታብ እንደተረከው፦ ነብዩ (ሰላም በርሱ ላይ ይሁን) ሰው ሚስቱን የሚደበድብበት ምክንያት ሊጠየቅ አይገባውም አለ። (ሱናን አቡ ዳውድ መጸሃፍ 11 ቁጥር 2142)

ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 4፥34 ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው ፤ አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው። መልካሞቹም ሴቶች (ለባሎቻቸው) ታዛዦች፥ አላህ ባስጠበቀው ነገር ሩቅን ጠባቂዎች ናቸው። እነዚያንም ማመጣቸውን የምትፈሩትን ገስጹአቸው፤ በመኝታቸውም ተለዩዋቸው፤ (ሳካ ሳታደርሱ) ምቱዋቸውም። ቢታዘዟችሁም፥ (ለመጨቆን) በነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ፤ አላህ የበላይ ታላቅ ነውና። 

አብደላ ኢብን አቡዱሁባብ እንደተረከው፦ ኡመር ወደ አላህ መልክተኛ (ሰላም በርሱ ላይ ይሁን) መጥቶ እንዲህ አለ፦ ሴቶች በባሎቻቸው ላይ ጠንክረዋል፤ እሱም (ነብዩ) እንዲደበድቡአቸው ፈቃድ ሰጠ። ብዙ ሴቶችም ወደ ነብዩ (ሰላም በርሱ ላይ ይሁን) ቤተሰቦች በመምጣት የባሎቻቸውን ስሞታ ያቀርቡ ጀመር። የአላህ መልእክተኛም (ሰላም በርሱ ላይ ይሁን) ብዙ ሴቶች ወደ ቤተሰቦቼ በመምጣት የባሎቻቸውን ስሞታ የሚያቀርቡት እነሱ ጥሩዎች አይደሉም አለ:: (ሱናን አቡ ዳውድ መጸሃፍ 11 ቁጥር 2141)

መሐመድ ቢ ቌስ አይሻ የተረከችውን እንደዘገበው፦ ,,, መሐመድ እንዲህ አለ፦ በፊት ለፊቴ ያየሁት ጨለማ ጥላሽ ነበርን? እኔም አዎ አልኩ። ደረቴንም መታኝ፥ አመመኝም። ከዚያም “ለመሆኑ አላህና መልእክተኛው ያለፍርድ የሚተውሽ ይመስልሻል?” ,,, (ሳሂህ ሙስሊም መጸሀፍ 004 ቁጥር 2127)

ኢክሪማ እንደተረከው፦ አይሻ እንዲህ አለች፥ አንዲት ሴት ከድብደባ የተነሳ እንደአረንጉአዴ የጠቆረ ሰውነቱአን እያሳየችኝ ባሏ ያደረሰባትን በደል ልትነግረኝ ወደ እኔ መጣች:: ,,, አይሻም ስትናገር፥ “እንደ አማኝ ሴት የተሰቃየች እኔ አላየሁም። ተመልከቱ! ቆዳዋ ከለበሰችው ልብስ ይልቅ አረንጓዴ ሆኖአል!” አብዱር ራህማን ሚስቱ ወደ ነቢዩ እንደሄደች በሰማ ጊዜ ከሌላ የወለዳቸውን ሁለቱ ወንዶች ልጆቹን ይዞ መጣ። ,,, አብዱር ራህማን አለ፥ “በአላህ ኦ አላህ መልክተኛ! ዋሽታለች! እኔ ጠንካራና እስዋን ማርካት የምችል ነኝ ነገር ግን አትታዘዘኝም ወደቀድሞ ባሉአ ሪፋ መመለስ ትፈልጋለች።” የአላህ መልክተኛ ለእስዋ እንዲህ አላት፥ “ፍላጎትሽ ይህ ከሆነ ከአብዱር ራህማን ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ሳታደርጊ ሪፋን መልሰሽ ማግባት እንደማትችይ ማወቅ ይገባሻል።” ,,,  (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቀጽ 7 መጽሃፍ 72 ቁጥር 715)

እንዚህ ተጎድታ ፍትህ ፍለጋ ወደርሱ የመጣችውን ይህችን ሴት ነብይ የተባለው መሐመድ ላሰቃያት ለባሏ መፍረድ እና ለእሱ መወገን ምን አይነት ግብረገብ ነው? ምን አይነትስ ፍርድ ነው?

መሐመድ ሴቶች የተፈጠሩት ጠማማ ሆነው፣ የወንድ ግማሽ አእምሮ ያላቸው፣ በድክመትና በጉድለት የተሞሉ እና ለወንዶች ፍላጎት ማስደሰቻ ናቸው እንዲሁም የሚገባቸው ውርስ የወንድን ግማሽ ነው ይለናል።

ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 2፥282 ,,, ከወንዶቻችሁም ሁለትን ምስክሮች አስመስክሩ፤ ሁለትም ወንዶች ባይሆኑ ከምስክሮች ሲሆኑ ከምትወዱአቸው የሆኑን አንድ ወንድና ፥ አንደኛዋ ስትረሳ አንደኛይቱ ሌላዋን ታስታዉሳት ዘንድ ሁለት ሴቶች ይመስክሩ,,,

አቡ ሳይድ አል-ኩድሪ እንደተረከው፦ ነቢዩ እንዲህ አለ፥ “የአንዲት ሴት ምስክርነት የአንድን ወንድ ምስክርነት ግማሽ ያህል አይደለምን?” ሴቶቹም፥ “አዎ።” እሱም፥ “ይህም የሆነው በሴቶች የአእምሮ ጐድለት ነው።” (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቀጽ 3 መጽሃፍ 48 ቁጥር 826)

እንደ መሐመድ ከሆነ ብዙዎቹ የገሃነም ነዋሪዎች ሴቶች ናቸው። ይህ የሆነበት ምክንያት ምንድነው ሴቶቹ አምላካቸውን ባለማመስገናቸው ነውን ተብሎ ሲጠየቅ፤ “የባሎቻቸውን መልካም ስራ አመስጋኞች አይደሉም። ምን መልካም ብታደርጉ እና እሷ መልካም ነገር ማየት ካልፈለገች፥ ከአንተ ምንም መልካም ነገር አላገኘሁም ትላለች::” (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቀጽ 2 መጽሃፍ 18 ቁጥር 161) (እንዲሁም ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቀጽ 1 መጽሃፍ 2 ቁጥር 29፤ ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቀጽ 7 መጽሃፍ 62 ቁጥር 125) በማለት መሐመድ ይመልሳል።

አቡ ሳይድ አል-ኩድሪ እንደተረከው፦ አንድጊዜ የአላህ መልክተኛ,,, እንዲህ አለ፥ “ሴቶች ሆይ! ብዙ የገሃነም ነዋሪዎች ሴቶች እንደሆኑ አይቻለሁና መስዋእትን አቅርቡ።” እነሱም ጠየቁ፥ “እንዴት ሊሆን ይችላል ኦ የአላ መልእክተኛ?” እሱም መለሰ፥ “እናንተ ሁልግዜ ትረግማላችሁ እንዲሁም ባሎቻችሁን አታመሰግኑም። በእውቀቱና በእምነቱ የበለጠ ደካማ የሆነ እንደ እናንተ ያለ ፍጡር አላየሁም። ,,,” ሴቶቹም ጠየቁ፥ “ኦ የአላህ መልእክተኛ! በእውቀታችንና በእምነታችን የጐደለው ምንድነው?” እሱም፥ “የሁለት ሴቶች ምስክርነት የአንድ ወንድ ምስክርነት ያህል አይደለምን?” እነሱም በማረጋገጥ መለሱ። እሱም፥ “ይህም የእውቀት ድክመቷ ነው። ሴት በወር አበባዋ ግዜ መጸለይና መጾም የማትችል አይደለችምን?” ሴቶቹም በማረጋገጥ መለሱ። እሱም፥ “ይህ ደግሞ የሀይማኖት ድክመቷ ነው።” (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቀጽ 1 መጽሃፍ 6 ቁጥር 301) (እንዲሁም ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቀጽ 2 መጽሃፍ 24 ቁጥር 541፤ ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቀጽ 3 መጽሃፍ 31 ቁጥር 172፤ ሳሂህ ሙስሊም መጸሀፍ 001 ቁጥር 0142)

አቡ ሁሬይራ እንደተረከው፦ ነቢዩ አለ፥ “ ,,, ወደገሀነም ተመለከትኩ እናም አብዛኛው ነዋሪዎች ሴቶች ነበሩ።” (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቀጽ 7 መጽሃፍ 62 ቁጥር 126) (እንዲሁም ሳሂህ ሙስሊም መጽሃፍ 036 ቁጥር 6596 እስከ ቁጥር 6601፤ ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቮሉይም 7 መጽሃፍ 62 ቁጥር 124፤ ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቀጽ 4 መጽሃፍ 54 ቁጥር 464፤ ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቀጽ 8 መጽሃፍ 76 ቁጥር 456)
በተጨማሪም መሐመድ ሴቶች የወንዶች ፍትወት ማርኪያ ንብረቶች ናቸው ይለናል። ለዚህም ማስፈራሪያ ሲጠቀም እንዲህ ይላል፥ “ወንድ ሚስቱን ወደ አልጋ ሲጠራት ለመምጣት እንቢ ብትል፥ መላእክቶች እስኪነጋ ድረስ እርግማናቸውን በርሷ ላይ ያወርዳሉ።” (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቀጽ 7 መጽሃፍ 62 ቁጥር 121) (እንዲሁም ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቀጽ 7 መጽሃፍ 62 ቁጥር 122፤ ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቀጽ 4 መጽሃፍ 54 ቁጥር 460፤ ሳሂህ ሙስሊም መጽሃፍ 008 ቁጥር 3367)
ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 2:223 ሴቶቻችሁ ለናንተ እርሻ ናቸው፤ እርሻችሁንም በፈለጋችሁት ኹኔታ ድረሱ፤ ለነፍሶቻችሁም (መልካም ሥራን) አስቀድሙ፤ አላህንም ፍሩ፤ እናንተም ተገናኝዎቹ መኾናችሁን ዕወቁ፤ ምእመናንንም (በገነት) አብስር።

መሐመድ ለወንዶች መሰቃየት ምክንያቱ ሴቶች ናችው እንዲሁም ሴቶች ለባሎቻቸው ታማኝ አለመሆናቸው በሄዋን የተነሳ ነው ይለናል። (ሂህ ሙስሊም መጽሃፍ 008 ቁጥር 3471 ና ቁጥር 3472 ሂህ ሙስሊም መጽሃፍ 036 ቁጥር 6603 ቁጥር 6604 ና ቁጥር 6606፣ ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 4 መጽሃፍ 55 ቁጥር 611)

በእናቶቻችንና በእህቶቻችን ላይ ይህን አይነት ግፍና በደል እንዲፈጸም የፈቀደውንና ያስተማረውን መሐመድን ሁሉን ቻይ ለሆነው ለእግዚአብሄር ነብይ ነው ብሎ መቀበል በጣም ይከብዳል።
 
ሸ) መሐመድ መጣልኝ ያለው መገለጥ ከራሱ፣ ከአምላክ፣ ወይስ ከሰይጣን?
መሐመድ መጣልኝ የሚለውን መገለጥ ከማን እንደሆነ ለመወሰን እስኪ ለመጀመሪያ ጊዜ መለአክ ከተባለው ፍጡር ጋር ያጋጠመውን ልምምድ እንመልከት።

አይ እንደተረከችው፥ ,,, መሐመድ እንደልማዱ በሂራ ዋሻ ውስጥ ብቻውን ሆኖ አላህን እያመለከ እያለ ,,, በድንገት መልአኩ ወደ እሱ መጥቶ እንዲያነብ ጠየቀው። ነብዩም ብ አልችልም ብሎ መለሰ።

ም ጨምሮ ሲናገር፥ “መልአኩ ልቋቋመው በማልችለው ሁኔታ በሃይል አንቆ ያዘኝ። ከዚያም ለቀቀኝና እንደገና እንዳነብ ጠየቀኝ። እኔም 'ብ አልችልም' ስል መለስኩለት። ዚህ ጊዜ እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ እስከማልችለው ድረስ ጨምቆ ያዘኝ። ለቀቀኝና እንደገና እንዳነብ ጠየቀኝ። እኔም መለስኩኝ፥ 'ብ አልችልም (ወይም ምን ላንብብ)?' እንደገና ለሶስተኛ ጊዜ እስከማልችለው ድረስ ጨምቆ ያዘኝና ሲለቀኝ እንደገና እንዲህ ሲል ጠየቀኝ፥ 'በጌታህ ስም ሁሉን በፈጠረ ሰውን ከረጋ ደም በፈጠረ አንብብ! ,,, " (96:1-3) ም የአላህ መልእክተኛ በድንጋጤ ልቡ በሃይል እየመታ ወደ ቤቱ ተመለሰ። ወደ ከድጃ ቢንት ኩዊልዲም መጥቶ፥ "ፍኝኝ! ሸፍኝኝ!" ት። እነሱም ፍርሃቱ እስከሚለቀው ድረስ ሸፈኑት,,, (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 1 መጽሃፍ 1 ቁጥር 3 ቅጽ 9 መጽሃፍ 87 ቁጥር 111)
መሐመድ ስለተሰማው ሁኔታ ለባለቤቱ ሲናገር፥ " ! ብርሃን ይታየኛል፣ ድምጽም ይሰማኛል፣ እንዲሁም አብጃለሁ ብዬ እፈራለሁ።" (ኢብን ሳድ፣ ገጽ 225)
ወደ መሐመድ የመጣው ይህ መንፈስ ከእግዚአብሄር ከሆነ፣ ለምን እራሱን በትክክል አልገለጸም? መንፈሱ/ፍጡሩ ለምን ጨመቀው፣ ለምን ኋይለኛ ሆነበት? ለምን ማንበብ እንደማይችልስ አላወቀም? እንደማይችል ካወቀስ ለምን አንብብ ብሎ ያስጨንቀዋል? ለመሆኑ መጽሃፍ ይዞ ነበር አንብብ ሲለው? ለምን መሐመድ መንፈሱን ከተገናኘው በኋላ በተረጋጋ ሁኔታ ከዋሻው አልተመለሰም? መደጡ ምናልባትም ለመጀመሪያ ጊዜ እንግዳ የሆነ ነገር በማየቱ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ለምን ይህ መንፈስ አይዞህ ብሎ አላጽናናውም? ለምን መሐመድ በደስታ እና በሰላም አልተሞላም?

በመጸሃፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሄርና መላእክቱ ገብርኤልን ጨምሮ ሰዎችን አነጋግረዋል። እነዚህ ሰዎች ግን እንደመሐመድ ሲፈሩና ሲናወጡ አናይም። መላእክቶቹም ማንንም በሃይልና በማስጨነቅ አልቀረቡም። የተላትን መልእክቱን የሚቀበሉትን ሰዎች ችሎታ ጠንቅቀው የተረዱ ነበሩ። 

በዘፍጥት መጽሃፍ ውስጥ እግዚአብሄር ኖህን ሲያናግረው (ፍጥ 6፡9-22፣ ምእ 7፣ 8፣ 9 ና 10) ኖህ ሲፈራ እና ሲናወጥ አናይም። እግዚአብር ሃይል ተጠቅሞ ኖህን አላስጨነቀውም ይልቁንም ኖህ እግዚአብሄር እንዲያደርግ የፈለገውን ጠንቅቆ ተረድቶ ነበር። 

እግዚአብሄር በተለያየ ጊዜ አብርሃምን አናግሮት ነበር (ፍጥት ምእራፍ 12 እስ ምእራፍ 18)። የደስታ ንግግር እንጂ ከእግዚአብሄርም ሆነ ከአብርሃም በኩል ምንም አይነት ግራ የሚያጋባ ድርጊት አናይም። እንዳውም አብርሃም የእግዚአብሄርን ፊት ሞገስ ከማግኘቱ የተነሳ እንኳን ሊፈራ ቀርቶ ስለወንድሙ ልጅ ስለሎጥ (ፍጥት 18፡22-33) ከእግዚአብሄር ጋር ሲደራደር እናያለን። ልክ እንደጓደኛ ነበር ከእግዚአብሄር ጋር ይነጋገር የነበረው።

እግዚአብሄር ሙሴን አናግሮት (ዘጸአት ምእራፍ 3 እስ ምእራፍ 34) ትእዛዝ ሲሰጠውና ለአዘዘውም የሚያስፈልገውን ነገር ሲያዘጋጅለት እናያለን።  እግዚአብሄር ራሱን ከገለጸለት በኋላ ለምን ወደ ግብጽ እንደሚልከው አስረድቶታል። ሙሴም እግዚአብሄርን ሲለየው በራስ መተማመን መንፈስና በፈቃደኝነት ነበር።

ሳያስ የእግዚአብሄርን ድምጽ ከሰማ በኋላ ራሱን ለእግዚአብሄር ሲያቀርብ፣ ሲፈወስና ከሃጥያቱም ሲነጻ እናያለን (ሳያስ ምእራፍ 6) እንጂ ሳያስ ግራ ሲጋባ አናይም።

መሐመድ ከመምጣቱ ስድስት መቶ አመት በፊት ገብርኤል ወደ ማርያም ተልኮ ነበር ( 1፡26-38) መለአኩም ንግግሩን በሰላምታ እንደጀመረ፣ ማርያምም ከሰላምታው እንደደነገጠች፣ መለአኩም አይዞሽ ብሎ እንዳጽናናት፣ መለእክቱንም ትህትና በተሞላበት ሁኔታ እንዳደረሰ፣ እሷም ከድንጋጤዋ ተረጋግታ ጥያቄ እንደጠየቀችውና ከእግዚአብሄር እንደተላከ የሚያሳይ ምልክት እንደነገራት እናነባለን። ንግግራቸውም ችግር ያለበት አልነበረም። ማርያም መጀመሪያ ላይ የደነገጠች ብትሆንም፣ መለአኩ አጽናናት እንጂ አላስጨነቃትም ወይም ሃይልን አልተጠቀመም። ከመረጋጋትም በላይ እንደቃልህ ይሁንልኝ ብላ ነበር የተለያዩት።

ይኸው መለአክ ገብርኤል ከሆነ ወደ መሐመድ የመጣው፣ ለምን ለማርያም ያሳየውን ትህትና ለመሐመድ አላሳየውም? አቀራረቡ ለምን ተቀየረ? ራሱን በማስተዋወቅ፣ ከየት እንደመጣ፣ ምን መልእክት እንዳመጣ በትህትና አልነገረውም እናም መሐመድ በደነገጠ ጊዜ ለምን አላጽናናውም? ለምን መቋቋም እስከማይችል ድረስ ጨመቀው፣ አስጨነቀው፣ እናም አስደንግጦት ከዋሻው ውስጥ አስሮጠው? ከዚህ ከመጀመርያው ልምምዱ በኋላ የአበደ እስኪመስለው ድረስ ሰላምንና እረፍትን ለምን አሳጣው?

የአላህ መልእክተኛ ሲናገር እንደሰማ ቢር ቢን አብደላ እንደተረከው፦ "በመድ ላይ ስሄድ ከሰማይ ድምጽ ሰማሁ። ቀና ብዬ ተመለከትኩ እና እንሆ! በሂራ ዋሻ ውስጥ የተገናኘኝ መለአክ በሰማይና በምድር መካከል በወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ነበር። ከዚያም ከመደንገጤ የተነሳ ወደ ባለቤቴ ገብቼ  'ልብስ ሸፍኑኝ! ሸፍኑኝ! አልኳቸው። ሸፈኑኝም,,,” (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 6 መጽሃፍ 60 ቁጥር 448)

እግዚአብሄር እና ከመላእክቱ ጋር ተነጋገሩ እንዲሁም ተገናኙ የተባሉት ሌሎች ነብያቶች ያልተለማመዱትን መሐመድ ግን ስለዚህ ፍጡር ያሳየውን አቀባበል፣ ፍርሃቱንና ሰላም ማጣቱን በመመልከት ይህ የተገናኘው መንፈስ ከእግዚአብሄር ነው ማለት እንዴት ይቻላል?

ከዚህም በላይ የመሐመድ መገለጥ ሁል ጊዜ የእሱን ፍላጎትና ምኞት እንደሚያሟላለት የተገነዘበችው የገዛ ሚስቱ አይሻ እንኳን ትዝብቷን እንዲህ ብላ ነበር የገለጸችው፥ “ጌታህ የአንተን ፍላጎትና ምኞት ለመሙላት ይጣደፋል።” (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 6  መጽሃፍ 60 ቁጥር 311)
መሐመድ ያሳደገውን ልጁን ሚስት ዘይነብን ማግባት በፈለገ ጊዜ ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 33፡37 ወረደልኝ ሲል፣ ከአራት ሚስት በላይ ማግባት በፈለገ ጊዜ ደግሞ ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 33፡50፣ እንዲሁም ሳውዳን ከሌሎች ሚስቶቹ ጋር በፍትህ ባላስተዳደራት ጊዜ ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 4፡128 ወርዶልኛል ብሎአል። እነዚህን የመሰሉ የመሐመድ አድሎአዊ የቁርአን ክፍሎችን በመመልከት ፍትሃዊ ከሆነ አምላክ የወረዱ ናቸው ማለት ያጠራጥራል?
መሐመድ አንንድ የቁርአን ክፍሎች ወረዱልኝ ያለው ሌሎች ካስታወሱትና ሃሳብ ከሰጡት በኋላ መሆኑን ስናነብ ደግሞ ከአምላክ ወረደልኝ የሚለውን አባባሉን ውድቅ ያደርገዋል። ኡመር፥ ሁለተኛው የእስልምና መንግስት አስተዳዳሪ (ካሊፋ) በሶስት ጉዳዮች ላይ የአላህ ቃል እንዲወርድ መሐመድን ካሳሰበው በኋላ መሐመድ ከአላህ ወረደልኝ እንዳለ በሃዲስ ተዘግቦ እናያለን። እነዚህም ሶስት የቁርአን ክፍሎች፦
1) በመካ ውስጥ የሚገኘውን ካባ የጸሎት ቦታ እንዲሆን (ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 2፡125)፣
2) የመሐመድ ሚስቶችና በአጠቃላይ ሴቶች እንዲከናነቡ/ሂጃብ እንዲለብሱ ማዘዝ (ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 24፡30-31፣ 33፡59 33፡53)፣
3) እንዲሁም መሐመድ በሚስቶቹ ባዘነና ወደእነሱ ለአንድ ወር ያህል ላለመግባት ቃል በገባ ጊዜ “ጌታው ከእናንተ የተሻሉ ሚስቶች ሊሰጠው ይችላል” የሚለውን የቁርአን ክፍል (ሱራ/ምእራፍ 66፡5) (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 1 መጽሃፍ 8 ቁጥር 395፣ ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 6ፍ 60 ቁጥር 10 እና ቁጥር 313፣ ሂህ ሙስሊም መጽሃፍ 031 ቁጥር 5903) ናቸው።
ከተለው ሃዲት ውስጥ ደግሞ መሐመድ አንድ አይነ ስውር ሰው ካስታወሰው በኋላ ቀደም ብሎ
መጣልኝ ላለው የቁርአን ክፍል ማሻሻያ ወረደልኝ ሲል እናያለን።

ዛይድ ቢን ታቢት፦ ነብዩ የሚጽፈውን ለዛይድ ሲነግረው፥ "ዝም ብለው የሚቀመጡት (ቤታቸው) አማኞች ለአላህ ሲሉ ከሚዋጉት ጋር እኩል አይደሉም።" ይድም በመቀጠል፥ መሐመድ ይህን በሚያጽፈኝ ጊዜ ኢብን ኡም ማክቱም እንዲህ አለ፥ " የአላህ መልእክተኛ! ህ፣ ይል ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ፣ ለአላህ ስል በተዋጋሁ ነበር።" ይህን ያለው አይነስውር ስለነበር ነው። ውም አላህ ለልእክተኛው ቁርአኑን ሲያወርድ ታፋውን በእኔ ታፋ ላይ አድርጎት ነበርና ክብደቱ እየጨመረ በመጣ ጊዜ ታፋዪ የሚሰባበር መስሎኝ ነበር። የነብዩ ይህ ሁኔታ እንዳለፈ አላህ የሚከተለውን ገለጸ፦ "ካለስንኩል ካልሆነ በስተቀር (ሉ የተጎዳ ወይም አይነስውር ወይም አንካሳ እና የመሳሰሉት) (ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 495)" (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 6 መጽሃፍ 60 ቁጥር 116) (እንዲሁም ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 6 መጽሃፍ 60 ቁጥር 117 እና ቁጥር 118፣ ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 4 ፍ 52 ቁጥር 85)

መሐመድና የእስልምና ተከታዮች ስለቁርአን ምንጭ ሲናገሩ፥ “ቁርአን ሁለት አወራረድ አለው። መጀመሪያ ከተጠበቀው ሰሌዳ በቅርቢቱ ሰማይ ወደሚገኘው ወደ ልቅናው ቤት በረመዳን ወር በከፍተኛይቱ ሌሊት በአንድ ጊዜ ለጅብሪል ወርዶአል። የመጽሃፉም ተራ አቀማመጥ በዚሁ አይነት ነው። ሁለተኛው አወራረድ በጅብሪል አማካይነት በነብዩ መሐመድ ላይ በ23 አመታት ውስጥ እንደ አስፈላጊነቱ እየተከፈለ ነው።” (ቅዱስ ቁርአን፣ ነጃሺ አሳታሚ ድርጅት፣ አ አ፣ አንደኛ እትም 1961 ሁለተኛ እትም ሚያዝያ 1997፣ መቅድም ቁጥር 8ኛ) ከላይ ያነሳናቸው መረጃዎች ቁርአን ከሰማይ ከነበረው ሰሌዳ ወረደ የሚለውን ማስተባበያ ውድቅ ያደርጉታል ወይም ከጥርጣሬ ያስገቡታል።

መሐመድን በዋሻ ውስጥ ያገኘውና ለሚቀጥሉት 23 አመታት ቁርአንን ያወረደለት ፍጡር ከእግዜአብሄር መሆኑ እርሱ ራሱ መሐመድ እንኳን የተጠራጠረው ጉዳይ ብቻ ሳይሆን አወረደልኝ ያላችውም የቁርአን ክፍሎች የራሱን ፍላጎትና ምኞት የሚያንጸባርቁና ሌሎች ካሳሰቡትና ሃሳብ ከሰጡት በኋላ ከአላህ ወረደልኝ ማለቱ በጣም የሚደንቅ ነገር ነው።        
ቀ) መሐመድ በአስማትና በመተት መጎዳቱ
ፍ ቅዱስ በእውነተኛ አማኞች ላይ አስማትና መተት ምንም ጉዳት እንደማያደርስ ይነግረናል። (ዘሁልቁ 23:23፣ ሉቃስ 10፡17-20)
ው ሃዲት መሰረት በመሐመድ ላይ አስማትና መተት ተሰርቶ የሚያደርገውን ነገር ማወቅ እስኪያቅተው ድረስ ሆኖ እንደነበር እንረዳለን። ከሚስቶቹ ጋር እንኳን ሳይተኛ አብሮአቸው የተኛ ይመስለው ነበር።
አይ እንደተረከችው፦ አስማት በአላህ መልእክተኛ ላይ ተደርጎበት ከሚስቶቹ ጋር ሳይተኛ ግንኙነት ያደረገ ይመስለው ነበር። ,,, (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 7 መጽሃፍ 71 ቁጥር 660 እና ቁጥር 661 እና 658፣ ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 4 መጽሃፍ 53 ቁጥር 400)
ከተሉት የቁርአን ክፍሎች መሰረት እውነተኛ የአላህ አገልጋዮችንና አማኞችን ሴጣንና የሰይጣን አሰራር እንደማይጎዳቸው ይናገራል።
ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 16፡98-100 ቁርአንንም ባነበብህ ጊዜ ርጉም ከኾነው ሰይጣን በአላህ ተጠበቅ፤ እርሱ በነዚያ ባመኑትና በጌታቸው ላይ በሚጠጉት ለርሱ ስልጣን የለውምና። ስልጣኑ በነዚያ በሚታዘዙት ላይና በነዚያም እነርሱ በርሱ (ምክንያት) አጋሪዎች በኾኑት ላይ ብቻ ነው።

(እንዲሁም ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 20፡65-70 ያንብቡ።)
ይህ የቁርአን ክፍል እውነት ከሆነ ለምን መሐመድ በመተትና በአስማት ተጎዳ? መሐመድ የሚያመልከው አምላክ እውነተኛ ከሆነ መሐመድ የሚሰራውን እስከማያውቅ ድረስ እንዳይሆን ለምን አልጠበቀውም? መሐመድ እውነተኛና የታመነ ሆኖ ከነበረ ደግሞ እንዴት አላህ እንዲህ ላለ ውርደት አሳልፎ ይሰጠዋል?
ሌላው የምናነሳው ጥያቄ፣ ታዲያ በአንድ ወቅት ራሱን እንኳን ያላወቀውን መሐመድን ከአምላክ ወረደልኝ ያለው ቁርአን ታማኝነት አለው ብለን እንዴት ልንቀበል እንችላለን?

2)      የመሐመድ ያልተፈጸሙ ትንቢቶች

ዘዳግም 1820-22 ነገ ግን ይናገር ዘንድ ያላዘዝሁትን በስሜ በድፍረት የሚናገር ወይም በሌላ አማልክት ስም የሚናገር ነብይ፥ እርሱ ይገደል። በልብህም፦ እግዚአብሄር ያልተናገረውን ቃል እናውቅ ዘንድ እንዴት ይቻለናል? ብትል፥ ነብዩ በእግዚአብሄር ስም በተናገረ ጊዜ የተናገረው ነገር ባይሆን ባይመጣም፥ ያ ነገር እግዚአብሄር ያልተናገረው ነው፤ ነቢዩ በድፍረቱ ተናግሮታል እርሱን አትፍራው።
እስኪ የመሐመድን ትንቢቶች በቁርአንና በሃዲት የተጻፉትን እንመልከት።
ቁርአን ሱራ/ምእራፍ 48፡27 አላህ ለመልእክተኛው ሕልሙን እውነተኛ ሲሆን አላህ የሻ እንደሆነ ፀጥተኞች ኾናችሁ ራሳችሁን ለጭታችሁ አሳጥራችሁም የምትፈሩ ስትሆኑ የተከበረውን መስጊድ በእርግጥ ትገባላችሁ ያለውን በእርግጥ እውነት አደረገለት። ,,,
ይህንን ከላይ የተጠቀሰውን ትንቢት/ራእይ እንዲፈጸም መሐመድ ከመካ የጣኦት አምላኪዎች ጋር የራሱን መብት በመሻር “የሁዳይቢያ ስምምነት” የተባለውን ስምምነት መፈራረም ነበረበት። በዚህ ስምምነት መሰረት መሐመድ ወደ እስልምና የገቡትን ከመካ ጣኦት አምላኪዎች ወገን የሆኑትን ለመመለስ ከመስማማቱም በላይ የአላህ መልእክተኛ የሚለውንም የክብር ስሙን በስምምነት መዝገብ ላይ ላለመጠቀምም ተስማምቶ ነበር።   
አል ሚስዋር ቢን ማክራህማ እና ማርዋን እንደተረኩት፦ ,,, (መሐመድና ተከታዮቹ ወደ ካባ እንዳይገቡ የመካ ሰዎች በከለከሉአቸው ጊዜ) የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አለ፥ "የመጣነው ማንንም ልንዋጋ ሳይሆን ኡምራ ለመፈጸም ነው። ,,,”  ,,, ሱሃይልም ለነብዩ "የሰላም ስምምነት መፈራረም ይኖርብናል” አለ። ዚያም ነብዩ ጸሃፊውን ጠርቶ አለው፥ "ሩህሩህና መሃሪ በሆነው ህ ስም ብለህ ጻፍ።" ይልም አለ፥ "ሩህሩህ የሚለው ባይገባኝም ቀድሞ እንደምትጽፈው በስምህ ኦ አላህ ብለህ ጻፍ።" ,,,  ም፥ "ይህ የሰላም ስምምነታችን ከአላህ መልእክተኛ ከመሐመድ ጋር ነው።” ይልም መልሶ፥ "ህ፥ የአላህ መልእክተኛ ሆነህ ቢሆን ኖሮ ካባውን (ጥቁሩ ድንጋይ የሚቀመጥበት ቤት) ከመጎብኘት ባልከለከልንህ እንዲሁም ከአንተ ጋር ባልተዋጋን። ስለዚህ መሀመድ ቢን አብደላ ብለህ ጻፍ።” ነብዩም አለ፥ "ህ! እናንተ ባታምኑም እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ። መሐመድ ቢን አብደላህ ብለህ ጻፍ።" ,,, ከዚያም ሱሃይል አለ፥ " ጋ ወደእናንተ የገቡትን ሰዎችም እንድትመልሱልን የእናንተን እምነት የተከተሉም ቢሆኑ እንጠይቃለን።” ,,, (ሳሂህ አል-ቡኋሪ ቅጽ 3 መጽሃፍ 50 ቁጥር 891)
እስራኤልን ከግብጽ የባርነት አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ሙሴ ለፈርኦን ጥያቄ ተንበርኮአልን? እየሱስ ወደ አይሁዶች ቤተመቅደስ ለመግባት ሲል መሲህነቱን ክዶአልን? እውነተኞቹ ነብያትስ እግዚአብሄር ያሳያቸው ነገር እንዲፈጸም ሲሉ በራሳቸው መንገድ በመሄድ የማይሆን ቃል ኪዳን ገብተው አማኝ ወንድምና እህቶቻቸውን አሳልፈው ለጠላት ለመስጠት ሞክረዋልን?  
ሌላው ደግሞ መሐመድ ኮንስታንቲኖፕል እንደተሸነፈ በሰባት ወር ጊዜ ውስጥ ደጃል የተባለው የክርስቶስ ተቃዋሚ እንመጣ ትንቢት ተናግሮ ነበር። (ን አቡ ዳውድ መጽሃፍ 37 ቁጥር 4281፣ 4282፣ እና 4283)

ኮንስታንቲኖፕል በ1453 እንደ ኤሮፓውያኖች አቆጣጠር ከተሸነፈ 7 ወር ብቻ ሳይሆን ወደ 5 ምእተ አለም አልፈዋል ግን ደጃል ገና አልመጣም። በዚህ መሰረት የመሐመድ ትንቢት እንዳልተፈጸመ እና ተጨባጭ ያልሆነ እንደሆነ እንረዳለን። ይህም እንደሃሰተኛ ነብይ ያስቆጥረዋል።  
ምንም እንኳን የተፈጸሙ ትንብቶች የአንድን ሰው እውነተኛ ነብይነት የሚወስኑ ባይሆንም ያልተፈጸሙ ትንቢቶች ግን በእርግጠኝነት የሰውየውን ሃሰተኛ ነብይነት የሚናገሩ ናቸው።
ማጠቃለያ
መሐመድ እውነተኛ ነብይ ነውን ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ያስተማረውን ትምህርቱን፣ ያሳየውን ስነምግባር፣ እና የተናገራቸውን ትንቢቶች ከዚህ በላይ ባቀረብነው መረጃ ፈትነናቸዋል። መሐመድ ቁርአን ከእሱ በፊት ያሉትን መጽሐፍት የሚያረጋግጥ ነው ሲለን ስለራሱ ደግሞ ለተከታዮቹ እንከን የማይወጣልኝ ምሳሌ ነኝ እኔን ይከተሉ ይላል። በቁርአንና በሃዲት ያሉትን የመሐመድ አስተምህሮዎች ከሱ በፊት ካሉት መጽሃፍት ጋር የሚቃረኑና የእሱን ፍላጎትና ምኞት የሚያስፈጽሙ ናቸው። መሐመድ ሌሎች አማልክትን አምልኮአል ሰገዶላቸዋል ተከታዮቹንም እንዲሁ እንዲያደርጉ አስተምሮአል፣ ውሸትን አስተምሮአል፣ አመንዝሮአል፣ ስለመጨረሻው ሰአት እንግዳ የሆኑ ነገሮችን አስተምሮአል፣ ተቃዋሚዎቹን ተበቅሎአል ገድሎአቸዋል፣ በአስማትና በመተት ተጠቅቶ ነበር፣ እንዲሁም ያልተፈጸሙ ትንቢቶችን ተናገሮአል። በእነዚህ ምክንያቶች መሐመድን እንደ እውነተኛ የእግዚአብሄር ነብይ አድርገን ልንቀበለው ይከብደናል።
ግር ማስታወሻ፦
-          የተለያዩ ሃዲቶች የተወሰዱት፦ ከደቡብ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ (University of Southern California, CRCC Center for Muslim-Jewish Engagement Resources Religions Texts) http://www.usc.edu/schools/college/crcc/engagement/resources/texts/
-          ፍ ቅዱስ፣ የኢትዮጵያ መጽሃፍ ቅዱስ ማህበር፣ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ታተመ 1962
-          ቅዱስ ቁርአን፣ ነጃሺ አሳታሚ ድርጅት፣ አ አ፣ አንደኛ እትም 1961 ሁለተኛ እትም ሚያዝያ 1997